የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ
- ሉቃስ 10፥39 ለእርስዋም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፥ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች።
- ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰሙኝም፥ እስራኤልም አላዳመጠኝም። መዝ 81፡11
- እነሆ፥ ተራሮችን የሠራ፥ ነፋስንም የፈጠረ፥ የልቡንም አሳብ ለሰው የሚነግር፥ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ የሚረግጥ፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው። አሞ 4፡13 ከወዳጄ ከአብርሃም እሰውራለሁን? በገነት ከአዳምና ሄዋን ጋር ይነጋገር ነበር ያምላክን ድምፅ በገነት ሲመላለስ ሰሙ( ድምፅህን ሰምቼ ተሸሸግሁ) ዘፍ 3:8-10
- የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና ፤ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ፦ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል አልሁ። ዮሐ 16፡ 12
- በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል።የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና።
- በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄምማንም አይነጥቃቸውም ዮሐ 10:27-28
1. ድምፁን የሚያሰማን እርሱ ስልወደደን መሆኑን ማወቅ አለብን
- ስለዚህ እኅቶቹ ጌታ ሆይ፥ እነሆ የምትወደው ታሞአል ብለው ወደ እርሱ ላኩ። ኢየሱስም ማርታንና እኅትዋን አልዓዛርንም ይወድ ነበር። ዮሐ 11፡4
- ሕዝቡንም ወደዳቸው ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ናቸው፤ በእግሮችህም አጠገብ ተቀመጡ፤ ቃሎችህን ይቀበላሉ።ዘዳ 33፡3
- ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፥ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና።ዮሐ 15፤15
- መታጠቂያ በሰው ወገብ ላይ እንደምትጣበቅ፥ እንዲሁ ሕዝብና ስም ምስጋናና ክብር ይሆኑልኝ ዘንድ የእስራኤልን ቤት ሁሉ የይሁዳንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣብቄአለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን አልሰሙም። ኤር 13፡11 2.
2.ጌታን ወደ ቤታችንና ወደ ሁኔታችን ሁሉ መጋበዝ
ቁ 38 ወደ ቤቷ ጋበዘች ዮሐ 11፡3
የምትወደው ታሟል ብለው ጠሩ ዮሐ 12፡2 በዚያም እራት አደረጉለት እርሱም፦ እናንተ የማታስተውሉ፥ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ፤ክርስቶስ ይህን መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን? አላቸው።ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው።ወደሚሄዱበትም መንደር ቀረቡ፥ እርሱም ሩቅ የሚሄድ መሰላቸው።እነርሱ፦ ከእኛ ጋር እደር፥ ማታ ቀርቦአልና ቀኑም ሊመሽ ጀምሮአል ብለው ግድ አሉት፤ ከእነርሱም ጋር ሊያድር ገባ።ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው፤ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም፤ እርሱም ከእነርሱ ተሰወረ። ሉቃስ 24፤2-31
ጌታ ኔው የመጣው፤ኣብሮኣቸው፡ምንድነው ምታወሩት? ቢያውቅም እንድነግረው ይፈልጋል፤ኣታስተውሉም ኣላመናችሁም፤ተረጎመላቸው፤ጋበዙት ቃሉ ጣፈጣቸው ጊዜ ማሳለፍ ፈለጉ ፤ተቀመጠ፤ኣይናቸውን ኣበራ
3. PRIORITY ወደንና ፈቅደን እንድናደርገው ያስፈልጋል።
ምርጫዋ ነው መልካም እድል መርጣለች፤ጌታም መስክሮላታል
- በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በልጆች መካከል ነው።ከጥላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀመጥሁ፥ ፍሬውም በጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው።መሃልይ 2፥3
- ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው፥ ባሪያህም ወደደው።መዝ 119፡140
- ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ። መዝ 119፡162
- ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝ 1፡1-3
4. ወደ የሱስ እግር አጠገብ መጠጋት አለብን INTIMACY ዮሐ 12 ላይም በእግሩ አጠገብ ነበረች
- ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቱ ንጥር ወስዳ የኢየሱስን እግር ቀባች፤ በጠጕርዋም እግሩን አበሰች፤ ቤቱም ከናርዶስ ሽቱ ሞላ። ዮሐ 12፡3
- ማርያምም ኢየሱስ ወዳለበት መጥታ ባየችው ጊዜ በእግሩ ላይ ወድቃ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር አለችው። ዮሐ 11፡32
- ሕዝቡንም ወደዳቸው ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ናቸው፤ በእግሮችህም አጠገብ ተቀመጡ፤ቃሎችህን ይቀበላሉ። ዘዳ 33፡
- ኢየሱስም ይወደው የነበረ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ በኢየሱስ ደረት ላይ ተጠጋ፤ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ እርሱን ጠቅሶ፦ ስለማን እንደ ተናገረ ንገረን አለው።እርሱም በኢየሱስ ደረት እንዲህ ተጠግቶ፦ ጌታ ሆይ፥ ማን ነው? አለው።ዮሐ 13:23-25
- ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል መዝ 73፡28 ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝ 1፡3
በዚችም ከተማ በገማልያል እግር አጠገብ ያደግሁ፥ የአባቶችንም ሕግ ጠንቅቄ የተማርሁ ሐዋ 22፡3
5. NO DESTRUCTION ተቀመጠች በተሰበሰበ ልብ መሆን ማርታ በብዙ ነገር ትታወኪያለሽ ትጨነቂማለሽ
ሕዝቡንም ወደዳቸው ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ናቸው፤ በእግሮችህም አጠገብ ተቀመጡ፤ ቃሎችህን ይቀበላሉ። ዘዳ 33፡3
እነርሱ፦ ከእኛ ጋር እደር፥ ማታ ቀርቦአልና ቀኑም ሊመሽ ጀምሮአል ብለው ግድ አሉት፤ ከእነርሱም ጋር ሊያድር ገባ።ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው፤ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም፤ ሉቃ 24፡29
ለጌታ ልንሰጠው የምንፈልገው ነገር ምንድነው? ከብዙ ሩጫችን ይልቅ ማርያም በእግሩ ስር ለመስማት መምረጧን ጌታ የማይወሰድባት እድል ነው ብሎታል? ጌታን ለማዳመጥ ጥቂት ጊዜ ልንሰጠው እንችላለን?