Acticles

የሙላቱ ልክ ምን ያህል ነው?

የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ቆላ 3፥16

የእግዚአብሔር የሙላቱ ልክ ሊደረስበትና ሊታውቅ የማይችል ነው ግን የምናገኘው የኛን ዝግጅት ያክል ብቻ ነው

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3፥18-19 ስለዚህ ምክንያት በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ፤በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ፤ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ። በማለት ሙላት ማለት በንድ ጊዜ ሳይሆን የሚደረስበት ረጅም ጉዞና የእየእለቱን ትጋት የሚጠይቅ ጉዞ አድርጎ ያቀርበዋል።

የእግዚአብሔር ሙላትና የባለፀግነቱ መጠን ተለክቶ የማያልቅ ነው ።እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥም እንደሚል ቃሉ፤ ግን እኛ ከርሱ ለመቀበል ራሳችንን ያዘጋጀነውንና፤ ያመነውን፤እንዲሁም ድንኳናችንን ያሰፋነውን ያክል በረከት እንቀበላለን፤ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን ታሪክ በ2 ነገስት ምእራፍ 4 ላይ አለ፤

2 ነገስት 4፡1 ከነቢያትም ወገን ሚስቶች አንዲት ሴት፦ ባሌ ባሪያህ ሞቶአል፤ ባሪያህም እግዚአብሔርን ይፈራ እንደ ነበረ አንተ ታውቃለህ፤ ባለ ዕዳ ልጆቼን ባሪያዎች አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቶአል ብላ ወደ ኤልሳዕ ጮኸች። 2 ኤልሳዕም። አደርግልሽ ዘንድ ምን ትሻለሽ? በቤትሽ ያለውን ንገሪኝ አላት። እርስዋም፦ ለእኔ ለባሪያህ ከዘይት ማሰሮ በቀር በቤቴ አንዳች የለኝም አለች። 3 እርሱም፦ ሄደሽ ከጐረቤቶችሽ ሁሉ ከሜዳ ባዶ ማድጋዎችን ተዋሺ አታሳንሻቸውም አላት። 4 ገብተሽም ከአንቺና ከልጆችሽ በኋላ በሩን ዝጊ፥ ወደ እነዚህም ማድጋዎች ሁሉ ዘይቱን ገልብጪ የሞላውንም ፈቀቅ አድርጊ አለ። 5 እንዲሁም ከእርሱ ሄዳ በሩን ከእርስዋና ከልጆችዋ በኋላ ዘጋች፤ እነርሱም ማድጋዎቹን ወደ እርስዋ ያመጡ ነበር፥ እርስዋም ትገለብጥ ነበር። 6 ማድጋዎቹም በሞሉ ጊዜ ልጅዋን፦ ደግሞም ማድጋ አምጣልኝ አለችው፤ እርሱም፦ ሌላ ማድጋ የለም አላት ዘይቱም ቆመ። 7 መጥታም ለእግዚአብሔር ሰው ነገረችው፤ እርሱም፦ ሄደሽ ዘይቱን ሽጪ ለባለ ዕዳውም ክፈዪ፤ አንቺና ልጆችሽም ከተረፈው ተመገቡ አለ። ውሀን ከአንድ ትልቅ ከውቂያኖስ ለመቅዳት ብንፈልግ ብርጭቆ ከሆነ የያዝነው ያዘጋዝጀነውን ያክል ሞልተን እንሄዳለን ፤ጋሎን አዘጋጅተን ከሆነም እንደዚያው በርሜል ከሆነም እንደዚያው ውሃው አያልቅም ግን በተዘጋጀነው መጠን እንሞላለን።

1. በእግዚአብሔር ፀጋ በህይወታችን ወደፊት እየጨመርን በሄድን ቁጥር ማለትም የበለጠ ከቃሉ ጋር ቅርርብ ባደረግነው መጠን ይበልጥ በጌታ ፊት በፀሎት በተጠጋን መጠን ቃሉን የመረዳታችን ጥልቀትም ይጨምራልን።

2. ቃሉ በህይወታችን እንዲያልፍ በፈቀድንለት ሁሉ ህይወታችንን ፍሬያማ ያደርገዋ

3. ቃሉ በኑሮአችንና በህይወታችን መንፈሳዊ ስጋዊም ፈውስ ያመጣል ህይወት ስለሆነ ለሞተው ነገራችን ህይወትን ይሰጣል ለዚህም ህዝቄል 47 ን ማየት ይጠቅማል።

ትንቢተ ሕዝቅኤል 47 መዝሙር 1

1 ወደ መቅደሱም መዝጊያ መለሰኝ፤ እነሆም፥ ውኃ ከቤቱ መድረክ በታች ወደ ምሥራቅ ይወጣ ነበር፥

3 ሰውዬውም ገመዱን በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ ወጣ አንድ ሺህም ክንድ ለካ፥ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃም እስከ ቍርጭምጭሚት ደረሰ።

4 ደግሞ አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃውም እስከ ጕልበት ደረሰ። ደግሞም አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃውም እስከ ወገብ ደረሰ።

5 ደግሞ አንድ ሺህ ለካ ልሻገረውም የማልችለው ወንዝ ሆነ፤ ውኃውም ጥልቅ ነበረ፥ የሚዋኝበትም ውኃ ነበረ፤ ሰው ሊሻገረው የማይችለው ወንዝ ነበረ።

6 እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ አይተሃልን? አለኝ። አመጣኝም፥ ወደ ወንዙም ዳር መለሰኝ።

7 በተመለስሁም ጊዜ፥ እነሆ፥ በወንዙ ዳር በዚህና በዚያ እጅግ ብዙ ዛፎች ነበሩ።

8 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ይህ ውኃ ወደ ምሥራቅ ምድር ይወጣል ወደ ዓረባም ይወርዳል ወደ ባሕሩም ይገባል፤ ወደ ባሕሩም ወደ ረከሰው ውኃ በገባ ጊዜ ውኃው ይፈወሳል።

9 ሕያው ነፍስ ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ ወንዙ በመጣበት ስፍራ ሁሉ በሕይወት ይኖራል፤ ይህም ውኃ በዚያ ስለ ደረሰ ዓሣዎች እጅግ ይበዛሉ፤ የባሕሩም ውኃ ይፈወሳል፥ ወንዙም በሚመጣበት ያለው ሁሉ በሕይወት ይኖራል።

11 እረግረጉና እቋሪው ውኃ ግን ጨው እንደ ሆነ ይኖራል እንጂ አይፈወስም።

12 በወንዙም አጠገብ በዳሩ ላይ በዚህና በዚያ ፍሬው የሚበላ ዛፍ ሁሉ ይበቅላል፥ ቅጠሉም አይረግፍም ፍሬውም አይጐድልም፤ ውኃውም ከመቅደስ ይወጣልና በየወሩ ሁሉ የፍሬ በኵር ያገኛል፤ ፍሬውም ለመብል ቅጠሉም ለመድኃኒት ይሆናል። መዝ 1

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፥18 መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤ ወደ ሙላቱ መድረስ የአፍታ ጉዳይ ሳይሆን ርጅም ጉዞ ነው ትጋት የሚጠይቅ የእየለቱ ሩሮ ነው።

4. የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ከሌለን ሌላ የህይወታችንን አቅጣጫ የሚመራ ነገር ይኖራል፤ 5. ከውጭ ማለትም ከሰይጣንና ከዚህ አለም የሚመጣብንን ፈተና መቋቋም አቅም እናጣለን፤ 6. በመንፈሳዊ ህይወታችን አናድግም

7. በትምህርት ነፋስ ለመወሰድ ምቹ እንሆናለን

ቃሉን ለመሞላት ሰው እጁን ጭኖ ስለፀለየልን የሚሆን ታምራዊ ነገር አይደለም፥ወይንም በየእሁዱ ከሰባኪ የምናገኘውም ኣይበቃም፤ እንዲሁም በካሴትና በሲዲ ስብከት ማዳመጥ ብቻም አይሆንም። ለዚያውም የምንሰማው ሁሉ ጤናማ ትምህርት ከሆነ።ሆኖም ልክ የእስራኤል ልጆች መና ለመልቀም በየማለዳው ይወጡ እንደነበረ፤ በየእለቱ እግዚአብሔር እንዲናገረን እየፀለይን ራሳችን በቀጥታ በጌታ ስር ሆነን መፅሐፍ ቅዱሳችን ጋር የፀጥታ ጊዜ ማጥፋት ይጠበቅብናል

  • ቃሉን መስማት
  • ቃሉን ማንበብ
  • ቃሉን ማሰብና ማሰላሰል
  • ቃሉን በልባችን መሰወር
  • ቃሉን ከህይወታችን ጋር በዕምነት ማዋሃድና ማድረግ ይጠበቅብናል።